Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢምፔሪያል ተሻጋሪ ድልድይ ፕሮጀክትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢምፔሪያል ተሻጋሪ ድልድይ ፕሮጀክት ያለበትን ደረጃ ጎብኝተዋል፡፡
 
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥ “የከተማ አስተዳደራችን በተለያዩ አካባቢዎች በ 2 ነጥብ 78 ቢሊየን ብር እየገነባቸው ካሉ 6 ዘመናዊ የመሸጋገርያ ድልድዮች መካከል የኢምፔሪያል ተሻጋሪ ድልድይ ፕሮጀክት ያለበትን ደረጃ ጎብኝተናል” ብለዋል።
 
ፕሮጀክቱ በአካባቢው ቀድሞ የነበረውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ በማስቀረት የትራፊክ ፍሰቱን በማሳለጥ እና ለከተማዋም አድገት የራሱ የሆነ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑንም አንስተዋል፡፡
 
ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን ይደረጋል ያሉት ከንቲባ አዳነች፥ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስና አበባ የማድረግ ጉዟችን በሁሉም መስክ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.