Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እና የጂቡቲን የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከር ያለመ ፎረም ተመሠረተ

አዲስ አበባ ህዳር 4፣2015 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ እና የጂቡቲን የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከር ያለመ የቢዝነስ ለቢዝነስ እና የመንግሥት ለቢዝነስ ፎረም ተመስርቷል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የመንግስት ሀብት ክላስተር አስተባባሪ ዶክተር ግርማ አመንቴ የተመራው ልዑክ እና የጂቡቲ ንግድ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዩሱፍ ሙሳ ዳዋለህ የሁለቱን ሀገራት የጋራ ፎረም አስጀምረዋል፡፡

በጂቡቲ የተመሰረተው ፎረሙ የኢትዮጵያ እና የጂቡቲን ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለማጠናከር ያለመ ነው ስለመባሉ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.