Fana: At a Speed of Life!

በሩብ ዓመቱ የተገኙ ድሎችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና ክፍተቶችን ለማስተካከል ርብርብ ማድረግ ይገባል – ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም የተገኙ ድሎችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን በአጭር ጊዜ ለመሙላት የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ ይገባል ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ገለጸ፡፡
 
ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ዛሬ በተካሄደው የመስተዳድር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸምን መገምገሙን አንስተዋል፡፡
 
በግምገማ መድረኩም የሴክተር መሥሪያ ቤቶች እቅድ አፈጻጸም የሚበረታታ መሆኑን አይተናል ነው ያሉት።
 
የክልሉ እቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ የተደረገው ግምገማ ስኬቶችን ለማስፋትና ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት ለመፍትሔ ለመዘጋጀት እድል የሰጠ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
 
በቀጣይ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሁሉም ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ ይገባል ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
 
በመሆኑም በሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም የተገኙ ድሎችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን በአጭር ጊዜ ለመሙላትም የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.