Fana: At a Speed of Life!

በንግድ ሥራ ፈጠራና ኢኖቬሽን ዘርፍ ንቅናቄ ለመፍጠር በተሠሩ ተግባራት ላይ ውይይት ተካሔደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በንግድ ሥራ ፈጠራና ኢኖቬሽን ዘርፍ ሀገራዊ ንቅናቄ ለመፍጠር በተከናወኑ ተግባራት ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ውይይት ተካሔደ፡፡

ውይይቱ የተካሔደው÷ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ እና የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በተገኙበት ነው፡፡

በንግድ ስራ ፈጠራና ኢኖቬሽን ዘርፍ ሀገራዊ ንቅናቄ ለመፍጠር የሚያስችሉ ሥራዎችን በመለየት ባጠረ ጊዜ ወደ ተግባር ለመቀየር እንዲቻል ያለመ ነው ውይይቱ፡፡

ዶክተር በለጠ ሞላ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት÷ በሀሳብና በጅምር ላይ ያሉ የምርምርና የፈጠራ ስራዎችን ወደ አንድ አምጥቶ በተቀናጀ የአሰራር ስርዓት ውስጥ በማስገባት ከድርጅቶች ጋር በመነጋገር ስራ ለመፍጠር የሚኒስቴሮቹ ሚና ከፍተኛ ነው።

ሀገራዊ ንቅናቄ በመፍጠር የስራ ፈጠራ ባህል ለመገንባት እና ውይይቶቹን ወደ ተግባር ለመለወጥ ዝግጁ ነን ማለታቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው÷ የኢኖቬሽን ሥነ-ምኅዳር ለመፍጠርና ያሉትንም ለማስፋት ሚኒስቴሮቹ በተናጠል የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ወደ አንድ ማምጣት ይገባል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያን ዐውድ የጠበቁ ችግር ፈቺ የፈጠራና ምርምር ሥራዎችን መተግበር የሚያስችል ማዕቀፍ መቅረጽ እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡

በውይይቱ መስማማት ላይ የተደረሰባችውን ሐሳቦች በማጠናቀቅ ወደ ተግባር ለመግባት ውሳኔ ተላልፏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.