Fana: At a Speed of Life!

22ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሰላም መጠናቀቁን ፖሊስ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የተካሔደው 22ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የፕሮግራሙ አዘጋጆች፣ አስተባባሪዎች እና የውድድሩ ተሳታፊዎች ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራታቸው በስኬት እንዲጠናቀቅ አስችሏል ብሏል ፖሊስ፡፡

ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ ሁሉ ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል፡፡

10 ኪሎ ሜትር እርቀት የሸፈነው 22ኛው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መነሻ እና መድረሻውን መስቀል ዐደባባይ አድርጎ መካሔዱ ይታወቃል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.