Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል እስካሁን 210 ሺህ ሄክታር መሬት ለበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ተለይቷል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በያዝነው ዓመት በአማራ ክልል በበጋ ወራት ለማልማት ከታቀደው 250 ሺህ ሄክታር የመስኖ ስንዴ ማሳ ውስጥ 210 ሺህ ሄክታር መሬት ተለይቶ መጠናቀቁን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አምሳሉ ጎባው፥ በዚህ ዓመት ክልሉ የስንዴ ምርቱን ለማሳደግ 250 ሺህ ሄክታር መሬት አዘጋጅቶ በዘር ለመሸፈን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

እስካሁን የልየታ ሥራው ከዕቅዱ 84 በመቶ መፈጸም መቻሉንም ጠቁመዋል።

ቀሪውን ልየታ ያልተከናወነበትን መሬት በአንድ ሳምንት ውስጥ ለመለየት እና ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በዚህ ልማት እንደ ክልል 10 ሚሊየን ኩንታል ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 2 ሚሊየን ኩንታሉ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ታቅዷል።

ይህንን ለማሳካት ከልየታ ስራው ጎን ለጎን የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ አቅርቦት ወደ ዞኖች ለማቅረብ ጥረት እየተደረገ ነውም ተብሏል።

አርሶ አደሩም በንቅናቄ የመኸር ሰብሉን ከሰበሰበ በኃላ በቀጥታ ለዚህ ልማት ዝግጁ እንዲሆን ዳይሬክተሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በሙሉቀን አበበ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.