አቶ ደመቀ መኮንን ከአልጄሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአልጄሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራመታን ላማምራን ጋር ተወያይተዋል፡፡
አቶ ደመቀ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ እና በደቡብ አፍሪካ ስለተፈረመው የሰላም ስምምነት ገለጻ አድርገዋል፡፡
ኢትዮጵያ ፈተና በገጠማት ወቅት አልጄሪያ ለወሰደችው በመርህ ላይ የተመሠረተ አቋም አቶ ደመቀ አመስግነዋል፡፡
ራመታን ላማምራን በበኩላቸው÷ የሰላም ስምምነቱ አፍሪካ የራሷን ችግር የመፍታት አቅም እንዳላት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ የግዛት አንድነት እና ደኅንነት እንዲከበር አልጄሪያ ትፈልጋለች ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
በውይይታቸውም የኢትዮ-አልጄሪያ ወዳጅነት እንዲጠናከር በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን ነገ በኒያሚ በሚጀምረው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ልዩ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አልጀሪያ ይገኛሉ፡፡