Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ 10 ቶን የሚመዝን የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኤርባስ አውሮፕላን አምራች ጅርጅት እና አቪዬሽን ሳንስ ፍሮንተርስ ከተሰኘ የፈረንሳይ ኩባንያ ጋር በመተባበር 10 ቶን የሚመዝን የህክምና ቁሳቁሶስ ድጋፍ አድርጓል።
 
ድጋፉን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ለጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስረክበዋል።
 
ድጋፉ ለተቸገሩ ወገኖች እና ለህክምና አገልግሎት የሚውሉ አልጋዎች፣ ወንበሮች፣ የተለያዩ አልሚ ምግቦች፣ ድንኳኖችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።
 
ድጋፉ ለጥቁር አንበሳ ሆስፒታልና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጓች የሚውል እንደሆነ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.