Fana: At a Speed of Life!

ኔይማር በጉዳት ምክንያት ከሁለት የምድብ ጭዋታዎች ውጭ መሆኑ ተረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጫዋች ኔይማር ጁኒየር በጉዳት ምክንያት በሁለት የምድብ ጭዋታዎች እንደማይሰለፍ ተገለፀ፡፡

ኔይማር ትናንት ምሽት ብራዚል ከሰርቢያ ጋር ባደረገችው ጨዋታ ላይ ባጋጠመው የቁርጭምጭሚት ጉዳት ምክንያት ነው ከሁለት የምድብ ጨዋታዎች ውጭ የሆነው፡፡

የብራዚል ብሄራዊ ቡድን ዶክተሮች ከሰርቢው ጨዋታ በኋላ የኔይማርን የጉዳት ሁኔት በተመለከተ ይፋ ባደረጉት የምርመራ ውጤት ተጫዋቹ ከሁለት የምድብ ጨዋታዎች ውጭ መሆኑን አስታውቀዋል።

የ30 ዓመቱ የፒ ኤስ ጂ ኮከብ በአሁኑ ሰዓት የፊዚዮቴራፒ ህክምናውን እየተከታተለ መሆኑን ስካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.