Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የምክር  ቤቱ  አፈ-ጉባዔ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ÷ጉባዔው የሰላም ስምምነት በተደረሰበትና የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የሌማት ትሩፋት እንደሀገር በተጀመረበት የሚካሄድ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

መንግስት ከህወሓት ጋር ያደረገው የሠላም ስምምነት  የክልሉ ምክር ቤት ሙሉ ለሙሉ የሚቀበለውና ለተግባራዊነቱ በቁርጠኝንት እንደሚሰራም ገልጸዋል።

አንዳንድ ሀገራት ሀገር ለመልማትና ለማደግ በምታደርገው ጥረት በሚዲያዎቻቸው ጭምር ተፅዕኖ ለማሳደር እየተጉ መሆኑንም  አስታውሰዋል፡፡

መሰል እንቅስቃሴዎችን ለመቀልበስ በአንድነት መተባበር እንደሚገባ ነው አፈ-ጉባዔዋ ያስገነዘቡት።

በግብርናው ዘርፍ በተለይም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በክረምት የተሰሩ የልማት ስራዎች በበጋውም ተጠናክረው መቀጠላቸውን አንስተዋል፡፡

በማዕድን፣ ቱሪዝም  እና በሌሎች ዘርፎች ያሉ እምቅ ሃብቶችን አልምቶ ለመጠቀም እንደ ክልል ትኩረት ተሰጥቶታልም ነው ያሉት።

በወንድሙ አዱኛ እና ፍቅረ ሚካኤል ዘየደ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.