Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሰራዊት አባላት በግዳጅ ቀጠናቸው ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የደረሱ ሰብሎችን ሰበሰቡ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ22ኛ ክፍለ ጦር የሰራዊት አባላት በግዳጅ ቀጠናቸው ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የደረሱ ሰብሎችን ሰብስበዋል።

የክፍለ ጦሩ ስነ-ልቦና ግንባታ ቡድን መሪ ሻምበል አዲሱ አለማየሁ ÷ከራስ በፊት ለህዝብ እና ለሀገር የሚለውን የተቋሙን እሴት በመላበስ ለህብረተሰቡ የገንዘብና የጉልበት ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ሰራዊቱ እየፈፀመ ካለው ወቅታዊ ተልዕኮ ጎን ለጎንም በግዳጅ ቀጠና ለሚገኙ አቅመ ደካሞች ሰብል በመሰብሰብ ድጋፍ መሳተፍ የሰራዊቱን ህዝባዊነት ማሳየት ነው ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች÷ ሰራዊቱ ከዚህ በፊትም በችግራቸው ደራሽ እና ደጋፊ መሆኑን ገልፀው ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.