Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ስፖርት ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)24ኛው የአማራ ክልል ስፖርት ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባዔ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

በጉባዔው 23ኛው የክልሉ ስፖርት ምክር ቤት ቃለ ጉባኤ የፀደቀ ሲሆን÷ የ2014 ዓ.ም የስፖርት ምክር ቤት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትም ቀርቦ ይገመገማል።

የምክር ቤቱ የ2015 በጀት አመት እቅድና በጀት እንደሚቀርብና በክልሉ ስፖርት ጉልህ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም እውቅናና ሽልማት የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል።

በሙሉጌታ ደሴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.