አቶ ደስታ ሌዳሞ በክልሉ የበጋ መስኖ ስንዴ ምርት መርሐ ግብርን አስጀመሩ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በሐዋሳ ዙሪያ ወረዳ ኡዶ ወጣጤ ቀበሌ የበጋ መስኖ ስንዴ ምርት መርሐ ግብርን በይፋ አስጀምረዋል።
አቶ ደስታ ሌዳሞ መርሐ ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት ÷ በክልሉ እርሻን ሜካናይዝድ የማድረግ እቅድን ስኬታማ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ፡፡
የእርሻ ስራን ለማዘመን ለተወሰኑ ሞዴል አርሶ አደሮች ትራክተር ተገዝቶ እንደተከፋፈለም ጠቅሰዋል፡፡
የአትክልት ስራዎችን በስፋት የማምረት ሂደት ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቁመው÷ለስንዴ ምርትም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።
የክልሉ የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ኃላፊ አቶ መስፍን ቃሬ በበኩላቸው፥የመስኖ ስራን ያለንን ዕድል ሁሉ አሟጦ በመጠቀም ዕቅዳችንን ማሳካት እንችላለን በለዋል።
በቀበሌው ለከርሰ ምድር ውሃ ቁፋሮ ብቻ 74 ሚሊየን ብር ወጪ መደረጉን ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ሌሎች ግብዓቶችን ለሟሟላትም 134 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጓል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡