በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ዘላቂ ሠላም ለማስፈን ያለመ ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዘላቂ ሠላም ለማስፈን ያለመ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
መድረኩ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን እና በከፍተኛ አመራሮች ልዑክ እየተመራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ባለፉት ዓመታት እንደ ሀገር ከፍተኛ የሆነ አለመረጋጋት የተፈጠረ ቢሆንም በህዝቦች አንድነትና በጸጥታ ኃይሉ ከፍተኛ መስዋዕትነት ክልሉ ወደ ሠላም ሊመለስ መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
በአሁኑ ወቅት አመራሮቹ ከመተከል ዞን ነዋሪች ጋር በዘላቂ ሰላም እና በዜጎች መልሶ ማቋቋም ዙሪያ ውይይት እያካሄዱ መሆኑ ተመላክቷል።
በውይይት መድረኩ ከግልገል በለስ ከተማ፣ከፓዊ ወረዳ፣ በማንዱራና ፓዊ ወረዳዎች የተውጣጡ የኅብረተሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።
በመተከል ዞን ለዘላቂ ሠላም ከፍተኛ አስተዋፅዖ ላበረከቱ አካላት ምሥጋና እና ዕውቅና መሰጠቱን የመተከል ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።