በመዲናዋ ህገ ወጥ የጎዳና ላይ የንግድ እንቅስቃሴ በሚያደረጉ አካላት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 1፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ አሳቻ ሰዓትን እየጠበቁ ህገ ወጥ የጎዳና ላይ የንግድ እንቅስቃሴ በሚያደረጉ አካላት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ንግድ ቢሮ ገለፀ።
የአዲስ አባበ ከተማ ንግድ ቢሮ መደበኛ ያልሆነ የንግድ ስርዓት ማስያዝ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳኛቸወ ሉሌ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ህገ ወጥ የጎዳና ንግድ ለኮሮናቫይረሰ መስፋፋት ከፍተኛአስተዋኦ አለው።
በዚህም ምክንያት በአዲስ አበባ አሳቻ ሰዓትን እየጠበቁ ህገ ወጥ የጎዳና ላይ የንግድ እንቅስቃሴ በሚያደረጉ አካላት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።
በተለምዶ ሰንደይ ማርኬት ተብሎ የሚጠራውን የግብይት እንቅስቃሴ ስፍራዎች ላይም የኮሮና ወርርሽኝ ለመከላካል በጥንቃቄ እንዲከናወን እየተደረገ መሆኑንም አቶ ዳኛቸው ተናግረዋል።
በከተማዋ ያሉ የንግድ ቦታወች የኮሮና ወርርሽኝን ለመከላከል ቢሮው ከጤና ባለሙያዎች ጋር በመሆን ክትትል እና ቁጥጥር እያደረገ እንደሆነም ጠቅሰዋል።
በቀጣይ የቁጥጥር ግብረ ሀይሉን በማጠናከር መልካቸውን ቀይረው በሚካሄዱ ህግ ወጥ የጎዳና ላይ ንግድን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ወደ ሰራ መግባቱን ቢሮው አስታውቋል።
በሲሳይ ጌትነት