ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የምግብና አልባሳት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን 1 ቢሊየን 47 ሚሊየን 909 ሺህ 135 ብር የሚያወጡ የተለያዩ የምግብና አልባሳት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።
ድጋፉ ለዘጠኙም ክልሎች እና ለሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ለ26 በጎ አድራጎት ማህበራት የተበረከተ ነው።
የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው የኮሮና ቫይረስ እያሳደረ የመጣውን ተፅዕኖ በጋራና በአብሮነት ለመከላከል እርዳታው አስፈላጊ መሆኑን በመጥቀስ ለሁለተኛ ጊዜ መደረጉን ተናግረዋል።
የተደረገው ድጋፍ በተለያየ ጊዜ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በኮንትሮባንድ መልክ የተያዙ መሆናቸው በርክክቡ ወቅት ተገልጿል።
ድጋፉን የየክልሉ አመራሮች እንዲሁም የሚመለከታቸው ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ከአቶ ላቀ አያሌው እና ከጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ እጅ ተረክበዋል።
በብስራት መንግስቱ