Fana: At a Speed of Life!

የበጎ ፈቃድ ደም ለጋሾች ቁጥር እየቀነሰ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጾም ወቅት የደም ለጋሾች ቁጥር ስለሚቀንስ በቂ ደም እያገኘ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ደም እና ህብረህዋስ ባንክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በተያዘው የጾም ወቅት በቂ ደም ከማግኘት አንፃር ውስነነት መኖሩን የኢትዮጵያ ደም እና ኅብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ታዬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

ሕይወትን ማትረፍ ከፆሙ ዓላማ አንፃር ያለው ፋይዳ ትልቅ ስለሆነ ከአፍጥር እና ከፆም ሰዓታት በኋላ ደም በመለገስ የደም ሕክምና የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች ለመታደግ ሕብረተሰቡ በንቃት ደም እንዲለግስ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ደም የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች ሕይወት ለመታደግ በተንቀሳቃሽ እና በቋሚ ቦታዎች ደም የማሰባሰብ ሥራው እየተሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በአዲስ አበባ ቅዳሜ አደባባይ ላይ ድንኳን በመትከል የበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾችን በመቀስቀስ እና እሁድ በቤተ እምነቶች የደም ማሰባሰብ ሥራ እየተከናነ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በሥራ ቀናትም በትምህርት ቤቶች፣ መንግሥታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት በመዘዋወር የደም ማሰባሰብ ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡

ሕብረተሰቡም የወገኑን ሕይወት ለመታደግ በንቃት ደም እንዲለግስ ጠይቀዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.