በሕገወጥ መንገድ የወርቅ አፈር ሲያዘዋውሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል በአኙዋክ ብሔረሰብ ዞን በዲማ ወረዳ በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ የወርቅ አፈር ከእነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር መዋሉን የዲማ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የምርመራ ክፍል ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ማስረሻ አበበ እንደገለፁት÷ በዛሬው ዕለት ከረፋዱ 4:30 አካባቢ መነሻውን ከአጌም ቻም የማዕድን ማውጫ ሳይት ያደረገ ተሽከርካሪ በሶስት የተቆረጠ በርሜል እና 28 የተቋጠረ ማዳበሪያ የወርቅ አፈር ጭኖ ዲማ ከተማ ውስጥ በህብረተሰቡ ጥቆማ ተይዟል።
በአሁኑ ሰዓት አሽከርካሪውን ጨምሮ በሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይም ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የወረዳው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!