Fana: At a Speed of Life!

193 ድርጅቶች የልዩ መብት የተፈቀደላቸው ኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች መርሐ ግብር ተጠቃሚ ሆኑ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን ለ193 ድርጅቶች “የልዩ መብት የተፈቀደላቸው ኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች መርሐ ግብር” ተጠቃሚ እንዲሆኑ እውቅና ሰጥቷል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት÷ ኮሚሽኑ የተጣለበትን ሃላፊነት ለመወጣት አሰራሮቹን የማዘመን ሥራዎችን እየሰራ ነው።

መርሐ ግብሩም የሎጅስቲክ አፈጻጸምን በማሻሻል እንዲሁም የጉምሩክ ሕግ ተገዥነትን በማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል።

ይህ ጥቅም የተሰጣቸው ድርጅቶች የተሰጣቸውን መብት በታማኝነትና በልዩ ጥንቃቄ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አሳስበዋል።

አገልግሎት ሰጭ የመንግሥት ተቋማት ድርጅቶቹ ለሚያቀርቧቸው ማናቸውም የቅድሚያ አገልግሎት ግልጽ አሰራር በመዘርጋት ተግባራዊ እንዲያደርጉም ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

ድርጅቶቹ በመርሐ ግብሩ መካተታቸው በማንኛውም የጉምሩክ አገልግሎት ፈጣንና ቅድሚያ አገልግሎት የማግኘት ዕድል ይፈጥራል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.