የበዓል ግብይት ፍትሐዊነትን የሚከታተል ግብረ ኃይል ወደ ሥራ ገባ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ መጭውን የትንሳኤ እና የኢድ በዓላት ምክንያት በማድረግ ፍትሐዊ የንግድ ፍሰትን የሚከታተልና የሚቆጣጠር ግብረኃይል ወደ ሥራ ገብቷል፡፡
የፍጆታ ምርቶች ላይ አላግባብ ጭማሬ በሚያደርጉ እና ምርትን በሚያከማቹ አካት ላይም ተገቢው እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጿል፡፡
ህብረተሰቡ በተገቢው መንገድ ግብይትን እንዲፈጽምና የምርት አቅርቦቱ ችግር እንዳይፈጠር በበቂ ሁኔታ አቅርቦት እንዲሰራጭ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታለ፡፡
የሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣ ንግድ ቢሮ፣ ፖሊስ፣ ኮሙኒኬሽን ቢሮ፣ ደንብ ማስከበር፣ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር እና ህብረት ስራ ኤጀንሲን ያካተተ የበዓል ህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥርና ክትትል ግብረ ኃይል ተቋቁም ወደ ሥራ ገብቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ እደገለጹት÷ በዓላቱን ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የሚደረግ የዋጋ ጭማሪ እና አላግባብ ምርት በሚያከማቹ ህገ ወጥ አካላት ላይ ክትትል እና ቁጥጥር በማድረግ ተገቢው ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!