8ኛው የውሃ ዲፕሎማሲ እና ተግባቦት ላይ ያተኮረ ፎረም እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 8ኛው የውሃ ዲፕሎማሲ እና ተግባቦት ላይ ያተኮረ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ባዘጋጀው በዚሁ ፎረም ላይ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር ) የዘርፉ ተመራማሪዎች፣ የህዳሴ ግድብ ተደራዳሪ ቡድን አባላት ተገኝተዋል።
በፎረሙ የውሃ ሃብቶችን መጠቀምን በተመለከተ መከተል በሚገባ የዲፕሎማሲ አካሄድና እና የተግባቦት ሁኔታ ላይ ምክክር እየተደረገ ነው።
ይህንኑ የተመለከቱ ጥናታዊ ፅሁፎችም በተመራማሪዎች በመቅረብ ላይ ይገኛሉ።
ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ያላትን የውሃ ሀብት ከመጠቀም ጋር በተያያዘ የገጠሙ የዲፕሎማሲ እና የተግባቦት ችግሮችን መፍታት የሚቻለው፥ ሀይልን አሰባስቦ መሰል መድረኮችን በማበርታት ሀሳቡ እንዲስረፅ በማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያን እውነተኛ የጋራ የመጠቀም ፍላጎት ለሌሎች ለማስገንዘብ በቅጡ የተገነዘበ ተቆርቋሪ መፍጠር ሲቻል በመሆኑ ሂደቱ ሊቀጥል እንደሚገባውም አስረድተዋል።
የውሃ ሀብቶችን ብቻ የተመለከቱ ምርምሮችና ሳይንሳዊ እውቀት የታከለባቸው የዲፕሎማሲና ተግባቦት አካሄድ የሚያርቁ አቅሞችን መፍጠር እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከተፈጥሮ ሀብቷ እንዳትጠቀም የሚፈልጉ ሀገራት በዘርፉ ያላቸው አቅምና የሰለጠነ የሰው ሀይል በዓለም አቀፍ መድረክ የእኛን የማስረዳት አቅም በልጦ ይገኛል ያሉት ሚኒስትሩ፥ ለዚህም ነባር ባለሙያዎችን ከአዳዲሶቹ ጋር በማቀናጀት ለብርቱ ስራ መዘጋጀት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
በሃብታሙ ተክለስላሴ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!