የሥርዓተ ምግብ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ ነው – ዶክተር ሊያ ታደሰ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የሥርዓተ ምግብ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የ2022 የዓለም አቀፍ የረሃብ መረጃ ኢንዴክስ ሪፖርት የግብርና ሚኒስቴር እና የጤና ሚኒስቴር ከአላያንስ 2015 አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ይፋ አድርገዋል፡፡
“የምግብ ሥርዓት ትራንስፎርሜሽን እና የታችኛው መዋቅር አስተዳደር” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ውይይት ላይ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡
መንግስት የምግብና የሥነ-ምግብ ፖሊሲን፣ ስትራቴጂን፣ የሰቆጣ ቃልኪዳንን እና የተለያዩ ፕሮግራሞችን በመተግበር ዜጎችን የምግብ ዋስትና ያላቸው ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አንስተዋል፡፡
የኢኮኖሚ ዕድገት ለማረጋገጥ፣ የሕፃናትን ሞት ለመቀነስ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የዚህ አይነት ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ መረጃዎች እጅግ አስፈላጊ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የግብርናና አትክልት ፍራፍሬ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መለሰ መኮንን (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ መንግስት ምግብና ሥነ-ምግብን በሚመለከት በክላስተር እርሻ፣ የስንዴ ምርት በማሳደግ እና በሌማት ትሩፋት እና በመሳሰሉት ትግበራዎችን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ከልማት አጋሮች ጋር በጋራ በመሆንም የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ተግዳሮቶችን የሚቀርፉ እና ምርትን የሚያሻሽሉ ስልት ማዘጋጀቱንም ገልጸዋል።
የ”አሊያንስ 2015” ተቋማትን ወክለው የ”ኮንሰርን ወርልድዋይድ” የኢትዮጵያ ተወካይ በሪፖርቱ ላይ ገለፃ ያቀረቡ ሲሆን የፓናል ውይይትም ተደርጓል።
በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፋን አውር በመዝጊያ ንግግራቸው፥ በኢትዮጵያ የወቅቱን ፈታኝ የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ ሁኔታ ድጋፍ በማድረግ ለማሻሻል ያለውን ቁርጠኝነት ማረጋገጣቸውንም ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!