ሁሉም በተሰማራበት መስክ ሀገርን ማስቀደም እንዳለበት አፈጉባዔ ታገሰ ጫፎ ገለጹ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁሉም በተሰማራበት መስክ ብሔራዊ ጥቅምን በማጠበቅ ሀገርን ሊያስቀድም እንደሚገባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ገለጹ፡፡
መገናኛ ብዙኃን ለብሔራዊ ጥቅም በሚል የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
አፈ ጉባኤ ታገሰ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ መገናኛ ብዙኃን ለብሔራዊ ጥቅም ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን፣ ብዝሃነት፣ ሠላም እና አንድነትን ከማስጠበቅ አንፃር መገናኛ ብዙኃን ከመንግስት ጎን በመሆን መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ሰይፈ ደርቤ÷ አዜአ በ2022 የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ድምፅ ለመሆን እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በመድረኩ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች እየተሳተፋ ነው፡፡
በሲሳይ ዱላ