Fana: At a Speed of Life!

የዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፉን ለማነቃቃት የሚረዳ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ እየተሰጠ ነው – ዶክተር በለጠ ሞላ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዲጂታል ኢኮኖሚ  ዘርፍን ለማነቃቃት የሚረዳ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ እየተሰጠ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር ) ገለጹ፡፡

የአውትሶርሲንግ ማህበር ምስረታ ማብሰሪያ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በማህበሩ የምስረታ ማብሰሪያ ፕሮግራም ላይ እንደገለጹት÷ የዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፉን ለማነቃቃት የሚረዳ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ እየተሰጠ ነው፡፡

በዘርፉ ከተሰማሩ ኩባንያዎች እና ማህበራት ጋር ለመስራት የመስሪያ ቤቱን ቁርጠኝነት ጠቅሰው የመስሪያ ቦታ እና የመሠረተ ልማት አቅርቦት ችግሮችን ለመቅረፍ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይ ሲ ቲ) ፓርክ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዲጂታል አገልግሎቱ ዘርፍ የስራ ፈጠራና የገበያ ትስስር እንዲኖር አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማትን የሚያፋጥኑ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ፣ በዲጂታል የንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች የትውውቅ፣ የትብብር እና የትሥሥር ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ልዩ ልዩ መደረኮችን በመፍጠር፣ ሀገራዊ የዲጂታል አገልግሎቶች እና ምርቶች ለህብረተሰቡ እንዲተዋውቁና ጥቅም ላይ እንዲውሉ አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግ ይገባልም ነው ያሉት።

በዲጂታል ላይ የተመሰረቱ ኦንላይን ግብይቶች እንዲስፋፉ የአስራር ስርአት መዘርጋትና ለግሉ ዘርፍ መሰረት የሚሆኑ ፖሊሲዎች፣ የዲጂታል ስትራቴጂዎች፣ ህጎች እና ሌሎች የአሰራር ስርአቶች ላይ ተገቢው ግንዛቤ እንዲፈጠር ማድረግ ይገባል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.