Fana: At a Speed of Life!

ከ111 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመጋቢት 22 እስከ 28 ቀን 2015 ዓ.ም በተደረገ ክትትል 88 ነጥብ 2 ሚሊየን የገቢ የኮንትሮባንድ እና 22 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር የወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ዕቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 18 ግለሰቦች እና 12 ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መወላቸውም ተገልጿል፡፡

አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድኃኒት፣ መዋቢያያዎች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች ከተያዙት ዕቃዎች መካከል መሆናቸውም ነው የተመለከተው፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት÷ ሞያሌ፣ ሐዋሳ እና አዲስ አበባ ኤርፖርት ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.