ሩሲያ አህጉር አቋራጭ የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች
ተተኩሶአዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ አህጉር አቋራጭ የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ በተሳካ ሁኔታ ማከናወኗን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚሳኤሉ ከደቡባዊ ሩሲያ ካፑስቲን ያር ተተኩሶ በካዛኪስታን ሳሪ ሻጋን በሚገኘው ክልል ውስጥ በታቀደለት መልኩ ማረፉ ተገልጿል።
“ሙከራው አዳዲስ የተፈጠሩ ስልታዊ የሚሳኤል መተግበሪያ ዘዴዎችን እና ቴክኒካል መፍትሄዎች ትክክለኛነትን ለማረጋገጥ አስችሎናል” ሲል የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል።
የሙከራው ዓላማም “ሙሉ በሙሉ በስኬት ተጠናቋል” ሲል ሚኒስቴሩ አያይዞ መግለፁን አር ቲ ዘግቧል።
ሙከራው የተካሄደው በዩክሬን የሞስኮ ወታደራዊ ዘመቻን ተከትሎ በሩሲያ እና በኔቶ መካከል ከፍተኛ ውጥረት በነገሰበት ወቅት ነው፡፡