የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ሰርቀዋል በተባሉ 4 ተጠርጣዎች ላይ ምርመራ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያለው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ሰርቀዋል በተባሉ አራት ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ኮተቤ አካባቢ በሚገኘው መብራት ኃይል ግቢ ውስጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ንብረትነቱ የቻይና ፓወር ኮንስትራክሽን የሆነ እና በግቢው ውስጥ ተቀምጦ የነበረ ከ5 ሚሊየን 900 ሺህ ብር በላይ ዋጋ ያለው የኤሌክትሪክ ሽቦ ማገናኛ ብረት በቻይና ፓወር ኮንስትራክሽን ሰራተኞች ተሰርቆ መወሰዱን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡
የየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባደረገው ክትትል ወንጀሉን ፈፅመዋል የተባሉ አንድ የድርጅቱን ሾፌር እና ሁለት የጉልበት ሠራተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተጠቁሟል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ከተያዙ በኋላ በተከናወነ ምርመራም ንብረቶቹን ለስራ የተፈለጉ በማስመሰል በተሽከርካሪ ጭነው በማውጣት በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ገላን ተብሎ አካባቢ በመውሰድ በአጠቃላይ በ64 ሺህ ብር ለአንድ ግለሰብ እንደሸጡ ተረጋግጧል፡፡
የተሰረቀውን ንብረት በማስመለስ እና ንብረቶቹን የገዛውን ግለሰብ ጨምሮ በአጠቃላይ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው የምርመራ መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!