Fana: At a Speed of Life!

ጥንቃቄ የሚሻው የበዓል ወቅት አመጋገብ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የበዓላት ወቅት አመጋገብ ተገቢው ጥንቃቄ ካልተደረገ ለጤና ችግር ሊዳርግ ይችላል፡፡

የጾም ቀናትን መጠናቀቅ ተከትለው በሚመጡ በዓላት ያለውን አመጋገብ ጥንቃቄ የተሞላበት ማድረግ እንደሚገባ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

ምክንያቱም ለረጅም ጊዜ ከቅባት ርቆ የቆየን ጨጓራ ለህመም የመዳረግ ዕድሉ ከፍተኛ ስለሚሆን ነው ይላሉ፡፡

ጥንቃቄ የጎደለው አመጋገብ ከሆነ÷ እንደ ሆድ መንፋት፣ የሆድ ቁርጠት፣ የጨጓራ ማቃጠል እና ሌሎችም ህመሞችን ሊያስከትል እንደሚችል ይገልጻሉ፡፡

በመሆኑም በዓላትን የጤና መታወክ ሳያጋጥም ለማሳለፍ÷ የሚዘጋጀው ምግብ በአግባቡ ንጽህናው የተጠበቀ መሆን ይኖርበታል ይላሉ፡፡

እንዲሁም ምግቦች ቅባት የበዛባቸው እንዳይሆኑ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድግ እንደሚያስፈልግ ነው የሚመክሩት፡፡

በአመጋገብ ወቅትም ቀስበቀስ ጨጓራን በማላመድ፣ በልክ እና ከመጠን ባላለፈ መልኩ ሊሆን እንደሚገባ ያነሳሉ፡፡

ጣፋጭ ምግቦችን እና የአልኮል መጠጦችን ከልክ በላይ ባለመውሰድ እራስን እና ቤተሰብን ከህመም መጠበቅ ይገባ ሲሉ ባለሙያዎች ይመከራል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.