የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ 1 ሺህ 200 ቤተሰቦች ለፋሲካ በዓል መዋያ የሚሆን ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በከተማዋ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ 1 ሺህ 200 ቤተሰቦች ለፋሲካ በዓል መዋያ የሚሆን ድጋፍ አደረገ።
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ የኮሮና ቫይረስ መከላከልና መቆጣጠር ግብር ሀይል ምክትል ሰብሳቢ አቶ አማረ ዓለሙ እንዳሉት፥ ለእነዚህ ቤተሰቦች 400 ሺህ ብር የሚያወጡ ለበዓል የሚያስፈልጉ እቃዎች ተከፋፍለዋል።
ለእያንዳንዱ ቤተሰብ ዶሮ፣ እንቁላል፣ ዙይት እና ሽንኩረት መከፋፈሉን ነው የገለፁት።
ድጋፉ የተገኘው የኮሮና ቫይረስ መከላከልና መቆጣጠር ግብረ ሀይል ከማህበረሰቡ ከሰበሰበው 8 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ውስጥ በመቀነስ የተሰጠ መሆኑን ምክትል ከንቲባው አስረድተዋል።
በተጨማሪም የተለያዩ ባለሀብቶች ለ200 ሰዎች ሰዎች ድጋፍ ማድረጋቸውንም ነው ያመለከቱት።
በናትናኤል ጥጋቡ