Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን ለማስፋፋት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል የተጀመረው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን ለማስፋፋት እየተሰራ መሆኑን የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡

የቢሮው ኃለፊ አቶ መምሩ ሞኬ ÷ በክልሉ ቆላ፣ ወይና ደጋና ደጋማ የአየር ፀባይ ባላቸው ወረዳዎች ዘንድሮ ስንዴ በመስኖ መልማቱን ተናግረዋል ፡፡

በእነዚህ አካባቢዎች ላይ የታየውን ምርጥ ተሞክሮ ወደ ሁሉም ወረዳዎች በማስፋት በክልሉ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ሥራን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በተለይ በየአካባቢው ያሉ የውሃ አማራጮችን ከወዲሁ በመለየት ለቀጣይ ዓመት የውሃ አቅምን አሟጦ በመጠቀም የበጋ መስኖ ስንዴ ልማቱን ለማስፋፋት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል ፡፡

በዘንድሮው በጋ በ1 ሺህ 632 ሄክታር ላይ ስንዴ በመስኖ መልማቱን ጠቅሰው ከዚህም በሄክታር በአማካይ 40 ኩንታል ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል፡፡

ዘንድሮ በበተከናወኑ  ሥራዎች በየትኛውም የክልሉ አካባቢዎች ስንዴን በመስኖ ማልማት እንደምንችል ትምህርት ወስደንበታል ያሉት ኃላፊው አንዳንድ አካባቢዎች በፍጥነት መሬቱን ማዘጋጀት አለመቻላቸው እንደ ተግዳሮት የሚነሳ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.