Fana: At a Speed of Life!

በጎርፍ አደጋ የሁለት ሕፃናት ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ሶዶ ከተማ ዋዱ ቀበሌ  በጎርፍ አደጋ የሁለት ሕፃናት ህይወት ማለፉ ተገለፀ፡፡

በቀበሌው ሶስት ህፃናት በጎርፍ መሄጃ ዲች ውስጥ በመጫወት ላይ ሳሉ ድንገት በጣለው ዝናብ ሁለቱ ህፃናት ወዲያው በጎርፍ መወሰዳቸው ነው የተገለፀው፡፡

አንደኛው ህፃን ግን መትረፍ መቻሉን የቀበሌው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር አስራት ፋልታ ተናግረዋል፡፡

በጎርፍ የተወሰዱት ህፃናት የሰባትና የዘጠኝ አመት እድሜ ያላቸው ሲሆን÷ በጎርፉ በግምት 1 ኪሎ ሜትር ያህል ከተወሰዱ በኋላ አስክሬናቸው መገኘቱ ታውቋል፡፡

ተመሳሳይ አደጋ እንዳይከሰት ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት መልዕክት ያስተላለፉት ሃላፊው  በመኖሪያ አከባቢዎች ያሉ ክፍት ዲቾች ሊከደኑ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በመለሰ ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.