Fana: At a Speed of Life!

የችግር ቀን ደራሽ የራስ አገርና ወገን መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው- ወይዘሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2012( ኤፍ.ቢ.ሲ) የችግር ቀን ደራሽ የራስ አገርና ወገን መሆኑን መገንዘብ ተገቢ መሆኑን የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ጠቅላይ አቃቤ ህጓ ይህን መልዕክት ያስተላለፉት የለይቶ ማቆያ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ሚኒስትሮች ጋር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በለይቶ ማቆያ የሚገኙ ወገኖችን በጎበኙበት ወቅት ነው።

የለይቶ ማቆያውን ኮሚቴው አባላት የሆኑት  ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣  የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም እና የማዕድና ነዳጅ ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ናቸው የጎበኙት።

በዚሁ ወቅት ሶስቱ ሚኒስትሮች የአንድ ወር ደሞዛቸውን በማዋጣት በዩኒቨርሲቲው በለይቶ ማቆያ አገልግሎት እየሰጡ ላሉ ባለሙያዎች ለፋሲካ በዓል 10 በጎችን አበርክተዋል።

ሚኒስትሮቹ በለይቶ ማቆያው በማገልገል ላይ ያሉትን የጤና ባለሞያዎች፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች እና የህግ አስከባሪዎችን በማግኘት እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.