Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከወገኔ የኢትዮጵያውያን ማኅበር የቦርድ አባላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በአሜሪካ በሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ከተመሰረተው ወገኔ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ቦርድ አባላት ጋርተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ 23 ዓመት ያስቆጠረው ድርጅት በአዲስ አበባ ችግር ውስጥ የሚገኙ ቤተሰቦችን በማገዝና ህጻናት ትምህርት እንዲያገኙ እየሠራ ስላለው የተቀናጀ የቤተሰብ ድጋፍ ገለጻ ተደርጓል፡፡

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ለቦርድ አባላቱ ለተነሳሽነታቸውና ላስገኙት ጥሩ ውጤት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በተጠናከረ ሁኔታ እንዲቀጥሉ ማበረታታታቸውንም የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.