የምስራቅ አፍሪካ እና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የፍልሰተኞች ጉዳይ የዳሰሳ ጥናት ሪፖርት ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ እና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የፍልሰተኞች ጉዳይ የዳሰሳ ጥናት ሪፖርት በናይሮቢ ይፋ ተደርጓል፡፡
የምስራቅ አፍሪካ እና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራትን የትብብር ማዕቀፍ በፍልሰተኞች አስተዳደርም ሆነ በሌሎች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች መጠናከር ለመላው አፍሪካ በአንድ የመቆም ምሰሶ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የሰዎች፣ የቁሳቁስ እና የአገልግሎት በነጻነት በቀጠናው መዘዋወር የኢኮኖሚና ማህበራዊ ትስስሩን ይበልጥ የሚያጠናክርና ለቀጠናው ሰላምና ደህነንት በጋራ የመቆም ዕድልን የሚያሰፋ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
ሪፖርቱ የቀጠናው ሀገራት በጋራና በተናጠል የፍልሰተኞችን ሁኔታ ህጋዊ መስመር ለማስያዝ የሚያደርጉትን ጥረት ወደ አንድ ለማምጣት ፍኖተ ካርታ ሆኖ የሚያገለግል ይሆናል ተብሏል፡፡
የጥናቱ ሪፖርት በዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት፣ በምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) እና የምስራቅ አፍሪካ ኮሙኒቲ በትብብር የተዘጋጀ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
በምስራቅ አፍሪካና በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የፍልሰተኞችን ሁኔታ በቅርበት በመከታተል፣ በማስተባበር እና በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ፍልሰትን በመደገፍ ለሚያደርጉት ድጋፍ የዓለም አቀፉን የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት፣ ኢጋድ እንዲሁም የምስራቅ አፍሪካ ኮሙኒቲን አመስግነዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!