በሩዋንዳ በጎርፍ አደጋ የ109 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ምሽት በምዕራባዊ ሩዋንዳ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ እስካሁን የ 109 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ፡፡
አደጋው የተከሰተው በምዕራባዊ ሩዋንዳ አካባቢ የሚገኘው የሴቤያ ወንዝ በመሙላቱ የተከሰተ ነው፡፡
ከጎርፍ አደጋው በተጨማሪ የመሬት መንሸራተት መከሰቱም ተጠቁሟል፡፡
በአደጋውም ሕይወታቸው ካለፈው ሰዎች በተጨማሪ በርካታ መኖሪያ ቤቶች መውደማቸው ተገልጿል፡፡
የሩዋንዳ ምዕራባዊ ግዛት አስተዳዳሪ ፍራንኮይስ ሃቢቴጌኮ ለሬውተርስ እንደተናገሩት÷ የነፍስ አድን ሥራዎች እየተከናወነ ነው፡፡