የፌዴራል ፖሊስ በሕገ-መንግሥቱ የተሰጠውን ሃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ ነው ተባለ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ፖሊስ በሕገ-መንግሥቱ መሠረት የተሰጠውን ሃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ መሆኑን የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ የፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ተቋሙ በሕገ-መንግሥቱ መሠረት የተሰጠውን ሃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ መሆኑን ከፍተኛ አመራሮቹ ገምግመዋል።
ከወቅታዊ ሀገራዊ የፀጥታ ጉዳይ ጋር የተገናኙ በርካታ ጉዳዮች ተነስተው ሰፊ ውይይት የተደረገባቸው መሆኑንም የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እና ሌሎች ከፍተኛ የተቋሙ አመራሮችም ከመድረኩ ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።
ከፍተኛ አመራሮቹ በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሰላምና ደህንነትን ለማስከበር እየተከናወኑ ያሉትን ተግባራት የበለጠ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በምክክር መድረኩ ላይ አንስተዋል።