Fana: At a Speed of Life!

1441ኛው የረመዳን ፆም አርብ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ታላቅ ቦታ ያለው የረመዳን ፆም የፊታችን አርብ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዬች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዬች ጠቅላይ ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት ሃላፈ ዑስማን አደም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገረት ጨረቃ ዛሬ ረቡእ ባለመታየቷ ፆሙ የሚጀመረው አርብ መሆኑን ገልጿል።

ወሩን በፆም እና ሀይማኖታዊ የፀሎት ስነስርአቶች የሚያሳልፉት ሙስሊሞች ራሳቸውንና ወገኖቻቸውን ከኮሮኖ ቫይረስ በመጠበቅ በቤት ውስጥና በመተሳሰብ እንዲያሳልፉ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር ኢድሪስ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ፆሙ አርብ የሚጀምር በመሆኑ ሀሙስ ምሽት የተራዊህ ሰላት የሚጀመር ይሆናል።
በሀብታሙ ተ/ስላሴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.