Fana: At a Speed of Life!

የእንስሳትና የዓሳ ሃብት ልማትን ለማሳደግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን መጠቀም ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የእንስሳትና የዓሳ ሃብት ልማትን ለማሳደግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በስፋት መጠቀም እንደሚገባ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ።

”የሌማት ትሩፋትን በመተግበር የስነ-ምግብ ዋስትናን እናረጋግጣለን” በሚል መሪ -ቃል  የግብርና ሚኒስቴር ያዘጋጀው የፓናል ውይይት በሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል።

በውይይት መድረኩ የተገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ÷ ኢትዮጵያ በእንስሳትና በዓሳ ሐብት የታደለች ሀገር ብትሆንም ከዘርፉ ብዙም ተጠቃሚ አይደለችም ብለዋል።

የግብርና ሚኒስትሩ  ግርማ አመንቴ  (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ በኢትዮጵያ ላሞች፣ ዶሮዎችና ከፍተኛ መጠን ያለው የንብ መንጋ ቢኖርም በቂ ወተት፣ እንቁላል፣ ማርና ዓሳ እየተገኘ አይደለም ብለዋል።

ለዚህም ዘመናዊ እርባታ አለመከተል፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ የአቅርቦት ችግርና ሌሎች ምክንያቶችን ጠቅሰዋል።

የዘርፉን ምርታማነት ለማሳደግ የሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብር ተግባራዊ ሆኖ በአጭር ጊዜ ውስጥ አበረታች ውጤት መገኝቱን አመልክተዋል።

የሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብር ከተጀመረ በኋላ በዘጠኝ ወራት ጊዜ ውስጥ ከ34 ሚሊየን በላይ የአንድ ቀን ጫጩቶች በዶሮ እርባታ ለተደራጁ ወጣቶች መሰራጨታቸውን ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ የንብ ቀፎዎች ለአርቢዎች ተሰራጭተዋል ማለታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.