Fana: At a Speed of Life!

የመጪው ክረምት የአየር ጸባይ ትንበያ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 ዓ.ም የበልግ የአየር ንብረት ግምገማ እና የመጪው ክረምት ወቅት የአየር ጸባይ አዝማሚያ ትንበያ ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፈጠነ ተሾመ÷በተለያዩ ቦታዎች ሊፈጠር የሚችልን የአየር ሁኔታ ገጽታ አስቀድሞ በመተንበይ የቅድመ-ማስጠንቀቂያና የትንበያ መግለጫዎች እየተሰጡ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ሕብረተሰቡም የሚተላለፉ መረጃዎችን እንዲጠቀምና የሚሰጠውን የቅድመ-ማስጠንቀቂያ መግለጫዎች በቅርበት አንዲከታተል አስገንዝበዋል፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ) በበኩላቸው÷ ባለፉት 3 ወራቶች ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ የጎርፍ አደጋ መሰል ተግዳሮቶችን ለመከላከልና ለመቀነስ አስተዋጽኦ የሚያደርግ የተጣጣመ የአየር ትንበያ መረጃ መሰጠቱን አንስተዋል፡፡

ሁሉም ባለድርሻ አካላትና ሕብሰተሰቡ መረጃውን በአግባቡ ከወሰደና ከተጠቀመ ተግዳሮቶችን በተሻለ ሁኔታ መቋቋም እንደሚቻል ነው የገለጹት፡፡

በቀጣይ ክረምት ወቅት ትንበያ ዙሪያ ሁሉም መገናኛ ብዙሃን ኢንስቲትዩቱ የሚሰጣቸውን ቅድመ ትንበያ መረጃዎችን ለዜጎች ተዳራሽ እንዲያደርጉ ማሳሰባቸውንም የሚኒስቴ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.