የወጣቶች የንግድ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ “ብሩህ ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል የንግድ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር እያካሄደ ነው።
አዳዲስ የንግድ ሃሳብ አመንጪ ወጣቶችን በማወዳደርና በመሸለም ውጤታማ የንግድ ፈጠራ ሃሳብ ይዘው ለሚመጡ ወጣቶች የስልጠና፣ የመነሻ ገንዘብና በንግድ ሥራ ብቁ እንዲሆኑ ድጋፍ ማድረግ የውድድሩ አላማ ነው ተብሏል፡፡
በውድድሩ የተሻለ የፈጠራ ሀሳብ ይዘው የመጡ ተወዳዳሪዎች እውቅና የሚያገኙበት መድረክ መሆኑን የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡