Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ በሸበሌ ዞን በጎርፍ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ነዋሪዎች ጎበኙ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ የተመራ ልዑክ በሸበሌ ዞን ቀላፎ ወረዳ በዋቢ ሸበሌ ወንዝ ሙላት ሳቢያ በጎርፍ ጉዳት የደረሰባቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች ጎበኙ፡፡

ልዑኩ በጎርፉ የተጎዱትን የግብርና ሠብሎች፣ ጤና ጣቢያዎችና ኅብረተሰቡ በሚኖሩባቸው የመኖሪያ ቤቶች ላይ ያደረሰውን ጉዳት መመልከታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህም በጎርፉ ጉዳት የደረሰባቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች የክልሉ መንግሥት ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት፣ከአየር ኃይል ፣ከለጋሽ ድርጅቶችና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚደረግ ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.