Fana: At a Speed of Life!

“ክኅሎት ለተወዳዳሪነት”10ኛው የመስተንግዶ እና የክኅሎት ሣምንት ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)”ክኅሎት ለተወዳዳሪነት” 10ኛው የመስተንግዶ እና የክኅሎት ሣምንት በአዲስአበባ ተከፈተ፡፡

የቱሪዝም ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት በየዓመቱ የሚያካሂደውን የመስተንግዶና የክኅሎት ሣምንት የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በቦታው በመገኘት አስጀምረዋል፡፡

ሚኒስትሯ የቱሪዝም ዘርፍ ትልቅ ትኩረት ከተሰጣቸው አምሥት ዘርፎች መካከል አንዱ መሆኑን በማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ ላይ አስታውሰዋል፡፡

በቱሪዝሙ ዘርፍ በአኅጉርም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን ብቃት ያለው የሰው ኃይል መፍጠር መሠረታዊ መሆኑንም ተናግረዋል።

ባለፉት 54 ዓመታት ቱሪዝም ኢንስቲትዩት በርካታ የዘርፉ ባለሙያዎች እንዲፈጠሩ ማስቻሉንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

የቱሪዝሙን ገበያ በማወቅ እና ሀገር በቀል ሐብቶችን በመጠቀም ዘርፉን ተወዳዳሪ ለማድረግ የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

የቱሪዝም ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በበኩላቸው፥ በ10ኛው የመስተንግዶ እና የክኅሎት ሣምንት ውድድሮች ዐውደ ርዕዮች እና ኮንፈረንሶች መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል፡፡

ሆቴሎች ባለሙያዎችን የሚመለምሉበት ዕድል መመቻቸቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.