Fana: At a Speed of Life!

ሀገራት በማዕድኑ ዘርፍ በኢትዮጵያ እንዲሠማሩ ጥሪ ቀረበላቸው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በማዕድኑ ዘርፍ በትብብር መሥራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

የኢፌዴሪ ማዕድን ሚኒስትር ሐብታሙ ተገኝ (ኢ/ር)፥ በጉዳዩ ላይ በኢትዮጵያ ከአውስትራሊያ አምባሳደር ጁሊያ ኒብሌት እና ከጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሲ አነጋግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ የሁለቱ ሀገራት የማዕድን ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በዘርፉ እንዲሰማሩ አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ለአምባሳደሮቹ አብራርተዋል፡፡

አምባሳደሮቹም በሀገራቸው የሚገኙ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በዘርፉ እንዲሰማሩ በጋራ ለመሥራት ፈቃደኞች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.