Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል የሕዝብ ለሕዝብ የኪነ-ጥበብ ድግስ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የሕዝብ ለሕዝብ ትሥሥርን ለማጠናከር ያለመ የኪነ-ጥበብ ድግስ በሐረሪ ክልል ተካሄደ።

ድግሱ የተዘጋጀው የቢፍቱ ኦሮሚያ ባንድ 30ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

መርሐ ግብሩ ለባንዱ መሥራቾችና ለባንዱ አባላት እውቅና ከመሥጠት ባሻገር የብሔር ብሔረሰቦችን አንድነትና ወንድማማችነትን ይበልጥ ለማጠናከር ያስቻለ መሆኑም ተገልጿል፡፡

የሐረሪ ክልል አፈ-ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድ ÷ ዝግጅቱ አንዱ የሌላውን እሴት እንዲያውቅ ፣ እንዲያከብር ብሎም የሕዝቦች የእርስ በእርስ ትሥሥር እንዲጠናከር ሚና አለው ማለታቸውን ከሐረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አብዱልሀኪም ሙሉ ÷ የሐረሪና የኦሮሞ ብሔረሰቦችን የሚያመሳስላቸው በርካታ ታሪካዊና ባሕላዊ ዕሴቶች እንዳሉ ጠቁመው ፣ መድረኩ እነኚህን እሴቶች ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።

የሀረሪ ክልል ባሕል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ ÷ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሠላም ፣ ብልጽግና እና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ነጻ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ ወንድማማችነት መጠናከር አለበት ብለዋል፡፡

የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ሁሴን ፈይሳ በበኩላቸው ÷ በክልሉ የተዘጋጀው የሙዚቃ ድግሱ የኦሮሞንና የሐረሪን ወንድማማችነት ይበልጥ ለማጠናከር ብሎም የጋራ የሆኑ ታሪካዊና ባሕላዊ ዕሴቶች ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ መሆኑን ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.