Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና የኮሎምቢያ የቱሪዝም ሚኒስቴሮች በዘርፉ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ዉይይት አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የቱሪዝም ሚኒስቴር ከኮሎምቢያ የቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በቱሪዝም እና ፕሮሞሽን ሥራዎች በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ዉይይት አድርገዋል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴዔታ ሠላማዊት ዳዊት ከኮሎምቢያ የቱሪዝም ምክትል ሚኒስትር አርቱሮ ብራቮ ጋር ነው የተወያዩት፡፡

በሁለቱ ሀገራት የቱሪዝም ዘርፍ ላይ የልምድ ልዉዉጥ ለማድረግና የቱሪዝም ምርቶችን በጋራ ማስተዋወቅ በሚቻሉባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል፡፡

ኮሎምቢያ በቱሪዝም ዘርፍ ትልቅ ልምድ ያላት ሀገር በመሆኗ የቱሪዝም ባለሙያዎችን ከማሠልጠን ጀምሮ የኢትዮጵያ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በኮሎምቢያ ለማስተዋወቅ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።

ሚኒስትር ዴዔታ አርትሮ ብራቮ በበኩላቸው ፥ ኢትዮጵያና ኮሎምቢያ በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጣቸው ምክንያት ለቱሪዝሙ ዘርፍ ትልቅ መስህብ የመሆን አቅም አላቸው ብለዋል።

ያላቸውን የቱሪዝም አቅምና ሐብት በተገቢው መንገድ ለማልማት ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ነው የገለጹት።

ሀገራቱ በቀጣይ የመግባቢያ ሠነድ ለመፈራረም ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.