የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ባለሐብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ባለሐብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ-ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ ቀረበላቸው፡፡
የኢፌዴሪ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ ÷ ከተባበሩት ዓረብ ኤሜሬቶች ባለሐብቶች ጋር ፍሬያማ ውይይት ማካሄዳቸውን ገለጸዋል፡፡
በውይይታቸውም ÷አዋጪ እና ክፍት በሆኑ የንግድ አማራጮች ላይ ገለጻ ማድረጋቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተጨማሪም ÷ኮሚሽነሯ መንግስት በዘርፉ ላይ ያደረገውን ማሻሻያዎች እና ማበረታቻዎች ለባለሃብቶቹ ማስረዳታቸው ተጠቁሟል፡፡