በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የክልል እና የዞን ምክር የጋራ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የክልል እና የዞን ምክር ቤቶች 2ኛ ዙር የጋራ የምክክር መድረክ በካፋ ዞን ምክር ቤት አዘጋጅነት በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በምክክር መድረኩ የ9 ወራት የክልል ምክር ቤት አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት ማድረግ፣ በካፋ ዞን በጊምቦ ወረዳ ጡላ ቀበሌ የተከናወኑትን የልማት ሥራዎች ጉበኝት በማድረግ የልምድ ልውውጥ እንደሚደረግ ይጠበቃል።
በመድረኩ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች የክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች፣ የብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች፣ የስድስቱም ዞኖች ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎች፣ ቋሚ ኮሚቴዎች እና የምክር ቤት አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክልል ከፍተኛ አመራሮች እና ክብር እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የምክክር መድረክ ለሁለት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል