Fana: At a Speed of Life!

የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎች የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎች በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይ ጎብኝተዋል።

“ከቤተ-ሙከራ ወደ አዝመራ” በሚል መሪ ሃሳብ በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀው የግብርና ሳይንስ ኢግዚቢሽን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተመርቆ ለተመልካቾች ክፍት መደረጉ ይታወቃል።

በአውደ ርዕዩ በግብርናው ዘርፍ የተለያዩ የምርምርና የፈጠራ ስራዎች፣ ዲጅታላይዜሽንና የግብርና ፋይናንስ ላይ ያተኮሩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ለዕይታ ቀርበዋል፡፡

አውደ ርእዩን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየጎበኙት ሲሆን÷ በዛሬው ዕለትም የተለያዩ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎች በስፍራው በመገኘት መመልከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አውደ ርዕዩ በግብርና ሚኒስቴር፣ በግብርና ትራስፎርሜሽን ኢንስቲትዩትና በኢትዮ-ቴሌኮም በጋራ የተዘጋጀ መሆኑ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.