በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚመክረው 64ኛው የኢጋድ ፎረም ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚመክረው 64ኛው የአፍሪካ ቀንድ የኢጋድ መድረክ “የአየር ንብረት ትንበያዎች አገልግሎት የመፍትሄ እርምጃ ለመውሰድ” በሚል መሪ ቃል ተጀመረ፡፡
በመድረኩ የቀጣናው የቀጣዮቹ አራት ወራት ማለትም የሠኔ ፣ ሐምሌ ፣ ነኀሤ እና መስከረም የአየር ንብረት ትንበያዎች እና ምልከታዎች እንደሚቀርቡ የኢጋድ ዋና ፀሃፊ ቃል አቀባይ ኑር ሞሐሙድ ሼክ አስታውቀዋል፡፡
መድረኩ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ረቡዕ በአዲስአበባ ይካሄዳል፡፡