Fana: At a Speed of Life!

ትምህርት በቤቴ” በሚል ተማሪዎች በቤታቸው ሆነው ትምህርታቸውን የሚከታተሉበት ስርዓት ተዘረጋ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትምህርት በቤቴ” በሚል ተማሪዎች በቤታቸው ሆነው ትምህርታቸውን የሚከታተሉበት ስርዓት መዘርጋቱን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ   እንደገለጹት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንዳይርቁ በማሰብ በቴሌቪዥን ፣በሬዲዮ እና በማህበራዊ ትስስር ገጾች በመታገዝ የትምህርት ክፍለ ጊዜዎች በመተላለፍ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ከባለፈው ሚያዚያ 07 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮም በአፍሪሄልዝ ቲቪ ከ7ኛ እሰከ 12ኛ ክፍል ድረስ ትምህርት ሙሉ በሙሉ መሰጠት መጀመሩን ሃላፊው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በኤፍ ኤም 94.7 እና ቴሌግራም እና ዋትስአፕ በመሳሰሉት ማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በሁሉም የትምህርት ክፍሎች የተለያዩ የትምህርት አይነቶችን ቀጥታ የማስተማር ስራ በመከናወን ላይ መሆናቸውን አቶ ዘላለም አንስተዋል፡፡

በአዲስ አበባ እና በዙሪያ ለሚገኙ ተማሪዎችም ተደራሽ ለማድረግ ከአማርኛ እና ከኢንግሊዘኛ በተጨማሪ በአፋን ኦሮሞ ትምህርቱ በመሰራጨት ላይ መሆኑን ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡

የትምህርት መርሃግብሩም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 3 – 6፡30 ከሰዓት ደግሞ ከ8 -9፡30 ሰዓት እንደሚሰጥ መገለፁን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.